Monday, May 12, 2014

ሪፖርተር ጋዜጣ ግንቦት 4, 2006 ዓ.ም

*ቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በ2004 ዓ.ም. የተጀመረው የሰበታ-ደወሌ አካል የሆነው ከመኢሶ እስከ ደወሌ የባቡር መስመር ዝርጋታ ሥራ ባለፈው ሐሙስ ሐዲድ በማንጠፍ ተጀምሯል፡፡


*ትዮጵያ በፓን አፍሪካ የታላቁ አረንጓዴ ግንብ ኮንቬንሽንን በማፅደቅ የሰሐራ በረሃ መስፋፋትን ለመግታት የሚታገሉ አገሮችን ልትቀላቀል ነው፡፡ 

*ትዮጵያ በየዓመቱ በአራት ከመቶ የከተሞች መስፋፋትና እ.ኤ.አ. በ2030 30 ከመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ሕዝብ በከተሞች ይኖራል ያለው የዓለም ባንክ፣ ለከተማ አስተዳደሮች የአቅም ግንባታ ይውል ዘንድ የ7.35 ቢሊዮን ብር ወይም የ380 ሚሊዮን ዶላር ብድር አፅድቋል፡፡ 


*ትዮ ቴሌኮም በአገሪቱ የነበረውን የቴሌ ኮም ሽፋን ለማስፋፋትና የአገልግሎቱን ጥራት ለማሳደግ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንም ለመትከል የ1.6 ቢሊዮን ዶላር ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሁዋዌና ዜድቲኢ ለተባሉት ሁለት የቻይና ኩባንያዎች ሰጥቷል፡፡ 

No comments:

Post a Comment